በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ባለቤቴ ፍትሕ እንዲሰጠው እጠይቃለሁ"- ወ/ሮ መቅደስ ለማ


መላኩ ፈንታ
መላኩ ፈንታ

በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ በአስቸኳይ ፍትሕ እንዲያገኙ ባለቤታቸው ወ/ሮ መቅደስ ለማ ጠየቁ።

አቶ መላኩ ፈንታ ጉዳያቸው ውሳኔ ሳያገኝ ላለፉት አምስት ዓመታት በፍርድ ቤት እየተመላለሱ መሆኑን ገልፀው አስቸኳይ ሕክምና የሚያስፈልገው የጨጓራ ቁስለት ታማሚ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

ልጆቻቸውንም ችግሩን በተረዱ ኢትዮጵያውያን እየተደገፉ በማስተማር ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል።

አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ከተነሱለት በሀገሪቱ ላይ ፍትሕ ከማስፈን ዓላማ አንፃር ጉዳዩ እልባት ያገኛል የሚል ተስፋ እንዳላቸውም ተናግረዋል።

የአቶ መላኩ ፈንታ ባለቤት ወ/ሮ መቅደስ ለማን ያነጋገረቻቸው ጽዮን ግርማ ተከታዩን ይዛለች።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ)

"ባለቤቴ ፍትሕ እንዲሰጠው እጠይቃለሁ"- ወ/ሮ መቅደስ ለማ
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:52 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG