የትግራይ ክልል የፀጥታ ሓይሎች በክልሉ ፖለቲካ ጣልቃ እየገቡ በመሆናቸው ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ሲሉ አራት የክልሉ ፓርቲዎች ጠየቁ::
ፓርቲዎቹ፣ ብሔራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ (ባይቶና)፣ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ፣ ውድብ ናፅነት ትግራይ እንዲሁም ዓረና ትግራይ ለዲሞክራሲ እና ሉዕላውነት ይህን የጠየቁት በጋራ በሰጡት መግለጫ ነው፡፡
በመግለጫቸውም በክልሉ ሰልፍ የሚከለክል ጥሪ በአዋጅ እና በሕግ ያልተደገፈ ነው ሲሉ ተቃውመዋል::
ትናንት እሁድ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ከነዋሪዎች ጋራ ለመወያየት በሽረ እንድስላሴ ከተማ የተጠራው ስብሰባ በተቃውሞ ግርግር መበተኑ ይታወሳል::
የክልሉ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ተኽላይ ፍቃዱ "የመንግስትን ስራ በሚያደናቅፉት ላይ ሕግ እናስከብራለን" ብለዋል::
መድረክ / ፎረም