በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና አሸናፊዎች ቤተሰቦቻቸውን አገኙ

በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክኒያት ከቤተሰቦቻቸው ጋራ በአካል ሳይተያዩና በስልክ ሳይሰማሙ ሁለት ዓመታት ያሳለፉ የትግራይ ተወላጅ አትሌቶች ዛሬ ከቤተሰቦቻቸው ጋራ ተገናኝተዋል። በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት አትሌት ደራርቱ ቱሉ የሚመራው ልዑክ አትሌቶቹን ከቤተሰቦቻቸው ጋራ ለማገናኘት ዛሬ መቐለ ከተማ ገብቷል፡፡ 53 አባላትን የያዘው ይህ ቡድን ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ዩጂን - ኦሬገን ላይ በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና አሸናፊዎች የነበሩት ለተሰንበት ግደይ፣ ጎተይቶም ገብረስላሴ እና ጉዳፍ ፀጋይን ያካተተ ነው።


ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG