በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጦር አካል ጉዳተኞች ከመቐለ ወደ ዓዲግራት የሚወስደውን መንገድ በተቃውሞ ዘግተው ዋሉ

የጦር አካል ጉዳተኞች ከመቐለ ወደ ዓዲግራት የሚወስደውን መንገድ በተቃውሞ ዘግተው ዋሉ

መቐለ ከተማ
መቐለ ከተማ
የጦር አካል ጉዳተኞች ከመቐለ ወደ ዓዲግራት የሚወስደውን መንገድ በተቃውሞ ዘግተው ዋሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:06 0:00

በትግራይ ክልል የቀድሞ ተዋጊ የጦር አካል ጉዳተኞች ዛሬ ማክሰኞ ታኅሣስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም. የክልሉ ዋና ከተማ መቐለን ከዓዲግራትና ሌሎች ከተሞች የሚያገናኘውን የተሽከርካሪ ማለፊያ መስመር በተቃውሞ ዘግተውት ዋሉ።

የጦር አካል ጉዳተኞቹ፣ “በትጥቅ ማስፈታትና የመልሶ ማቋቋም ሂደት ላይ ከሌሎች ሙሉ አካል ካላቸው የቀድሞ ተዋጊዎች ጋራ ተመድበናል በቂ ህክምናም እያገኘን አይደለም፣ አመራሮውቹ ረስተውናል” የሚሉና ሌሎች ተቃውሞዎችን በማስማት ከመቐለ ከተማ ሰላሳ ኪሎሜትር በምትርቀው አጉላዕ በተባለች ከተማ ላይ መንገድ ዘግተው ውለዋል።

ከትግራይ የጸጥታ ኃይሎች አመራር ሜጀር ጀነራል ማሾ በየነ ጋራ በጉዳዩ ላይ ከተወያዩ በኋላ መንገዱ ተከፍቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG