በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መራባቸውን የገለፁ የትግራይ ኃይሎችና የጦር ጉዳተኞች ዛሬ በመቀለ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ


መራባቸውን የገለፁ የትግራይ ኃይሎችና የጦር ጉዳተኞች ዛሬ በመቀለ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ
መራባቸውን የገለፁ የትግራይ ኃይሎችና የጦር ጉዳተኞች ዛሬ በመቀለ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ

በጦርነቱ ወቅት ጉዳት የደረሰባቸው ተዋጊዎች ሰልፉን ያካሄዱት ከተማዋ ምስራቃዊ አቅጣጫ ኲሓ መለስ ካምፓስ ከተባለ ስፍራ ተነስተው የክልሉ አስተዳደር ፅሕፈት ቤት በጦርነቱ ወቅት ጉዳት የደረሰባቸው ተዋጊዎች እስከሚገኝበት ከ15 ኪሎሜትሮች በላይ የሚሆን መንገድ በእግራቸው በመጓዝ ነው።

ጉዳተኞቹ በክራንች በመረዳት እና ሌሎች የአካል ጉዳተኞች አጋዥ መሳሪያዎችን ተጠቅመው ነው ሰልፉን ያካሄዱት።

ሰልፈኞቹ ከክልሉ ርእሰ መስተዳድር ፅህፈት ቤት ደጃፍ ተገኝተው ከህወሃት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር ተወያይተዋል::

ውይይቱ በድምፅም ሆነ በቪድዮ ለመቅረፅ አልተፈቀደም። ሰልፈኞቹ አደባባይ ወጥተው ድምጻቸውን ያሰሙበትን ምክንያት በውይይቱ ወቅት በተወካዮቻቸው አማካኝነት አሰምተዋል::

በመቶዎች የሚቆጠሩት ሰልፈኞች "ሰልፉን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ ተተኩሶብናል" ብለዋል:: "ዳቦ በመጠየቃችን ከ10 በላይ አስለቃሽ ጭስ ሊተኮስብን አይገባም። ይህን የፈፀሙ የፖሊስ አመራሮች በህግ ይጠየቁልን" ሲሉ ቅሬታቸውን ለአቶ ጌታቸው አሰምተዋል::

"ሰላም ለማምጣት የተዋጋን ዳቦ ማጣት የለብንም። ለኛ የተመደበ ምግብ በአመራሮች እየተወሰደ ነው።" ሲሉም ከሰዋል::

አደባባይ የወጣነው በአንድ ቀን ክስተት የተነሳ አይደለም። ለወራት ስንጠይቅ ቆይተናል። መልስ ባለማግኘታችን ነው አሁን ወደ ሰልፍ ለመውጣት የተገድነው።” ብለዋል::

"ጥያቂያችን በአፋጣኝ ይመለስልን። ላለፉት ሁለት ቀናት ምግብ አልቀመስንም።" ሲሉም ስላሉበት ሁኔታ አስረድተዋል::

አቶ ጌታቸው በበኩላቸው ለሰልፈኞቹ ሲናገሩ "በጀግንነት ተሰልፈው አካላቸው የጎደለ፣ ‘ምግብ አጥተናል’ ብለው ሰልፍ መውጣታቸው አሳዝኖኛል። ለዚህም ይቅርታ እጠይቃለሁ።" ብለዋል::

“ከነገ ጀምሮ ጥያቄዎቹን እንፈታለን” ያሉት አቶ ጌታቸው፤ “ይህ እንዲሆን ያደሩጉ ወገኖችን አጣርተን ተጠያቂ እናደርጋለን።” ብለዋል።አክለውም ሰልፉን ለመበተን ያለ አግባብ ኃይል የተጠቀሙ የፖሊስ አባላት ካሉም አጣርተን ተጠያቂ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል::

“ጥያቄው ከሰልፍ ይልቅ በሌላ ሕጋዊ መንገድ ቀርቦ ቢሆን ይመረጥ ነበር” ያሉት አቶ ጌታቸው፡ “ሆኖም ስሜታችሁን እንረዳለን” ለአሁኑ ምግብና ውሃ ወደምታገኙበት ስፍራ እንድትሄዱ ተሽከርካሪዎች

እየተዘጋጁ ናቸው” ሲሉ ከሰልፈኞቹ ጋር ያደረጉትን ውይይት ቋጭተዋል::

XS
SM
MD
LG