በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመቀሌ ከተማ መስተዳድር የመኖሪያ ቤቶች ችግር ለማቅለል እየሰራ ነው


ይኽ የአንድ ማህበር ፕላን ነው
ይኽ የአንድ ማህበር ፕላን ነው

የመቀሌ ከተማ መስተዳድር በከተማዋ የሚታየውን ከፍተኛ የመኖሪያ ቤቶች ችግር ለማቅለል ያስችላል ያለውን እርምጃ መውሰድ ጀምሯል፡፡

የመቀሌ ከተማ መስተዳድር በከተማዋ የሚታየውን ከፍተኛ የመኖሪያ ቤቶች ችግር ለማቅለል ያስችላል ያለውን እርምጃ መውሰድ ጀምሯል፡፡ በዚህም መሠረት በቤቶች ሥራ ማኅበራት ለተደራጁት አስራ አንድ ሺኽ አራት መቶ የቤተሠብ አስተዳዳሪዎች መሬት አስረክቧል፡፡ በሌላ በኩል ለቤቶቹ ግንባታ ሲባል የእርሻ መሬት የተወሰደባቸው አርሶ አደሮች ለመሬታችን ግምት የተሰጠን ካሣ በጣም ዝቅተኛ ነው በሚል ቅሬታቸውን እያሰሙ ነው፡፡

የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በተለይ ደሞ የመኖሪያ ቤቶች እጥረት በሰፊው በሚታይባት መቀሌ ከተማ ውስጥ በማኅበር ለተደራጁ ቤት ፈላጊዎች መሬት መስጠት ከአሥር ዓመታት በላይ አቋርጦት ቆይቷል፡፡

በአንፃሩ መሬት በሊዝ ማለትም በኪራይ ማወዳደር ቢቀጥልም አብዛኝው ጨረታ ውስጥ ገብቶ መወዳደር የማይችል ዝቅተኛ ገቢ ያለው ነዋሪ ለክፍተኛ የቤት ኪራይ ችግር ተጋልጧል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የመቀሌ ከተማ መስተዳድር የመኖሪያ ቤቶች ችግር ለማቅለል እየሰራ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:12 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG