ትላንት ረቡዕ ጥር 21 ቀን 2017 ዓ.ም በዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል ቡድን የተሾሙ ግለሰብ በትግራይ ክልል የመቐለ ኤፍ ኤም ራድዮ ጣቢያን ለመቆጣጠር መሞከራቸውን የጣቢያው ጊዜያዊ ሥራ አስከያጅ ገለጹ። ድርጊቱን ፈጽመዋል የተባሉ ግለሰብ ላይም ጣቢያው ክስ መመስረቱን ተናገሩ።
ጣቢያውን ሊቆጣጠሩ ነበር በሚል ወቀሳ ከቀረበባቸው ፣ አቶ ዘመንፈስቅዱስ ፍስሃ ምላሽ ለማግኘት በእጅ ስልካቸው ላይ በተደጋጋሚ ደውለን ስብሰባ ላይ መሆናቸው ስለገለፁን ምላሻቸውን ማካተት አልቻልንም።
ጉዳዩ ኣስመልክቶ ከመቐለ ፖሊስ አዘዥ ኮማንደር አንድነት ነገሰ ተጨማሪ ማብራርያ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ሆኖም የመቐለ ከተማ ፖሊስ መምርያ በፌስቡክ ገጹ በአወጣው መረጃ፣ ትላንት ረቡዕ ጥር 21 ቀን 2017 ዓ/ም በመቐለ ኤፍኤም 104.4 “የተሾመኩት እኔ ነኝ” በሚል የተነሳ፣ ጊዜያዊ አለመግባባት ተፈጥሮ እንደነበርና ፖሊሰ ሁኔታው ለማረጋጋት በቦታው ተገኝቶ እንደነበር አስታውቋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም