ዋሽንግተን ዲሲ እና መቀሌ —
በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ኢንደስትሪ ቀበሌ በተባለ ቦታ በተፈፀመ የአየር ድብደባ ስድስት ሰዎች መገደላቸው የአይደር ፊፈራል ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ክብሮም ገብረስላሴ ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ።
ከሟቾቹ መካከል ሦስቱ ሕፃናት መሆናቸውን ገልፀው፤ 21 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል ብለዋል።
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ በዛሬው ዕለት በመቀሌ ከተማ በሚገኘው መስፍን ኢንጂነሪንግ ላይ ለሁለተኛ ጊዜ የአየር ጥቃት መፈጸሙን ለቪኦኤ ተናግረዋል። ጥቃቱ የተፈፀመው አሸባሪው ያሉት የህወሃት ቡድን የጦር መሳሪያዎቹን ለመጠገን የሚጠቀምበት ቦታ ስለሆነ ነው ብለዋል።
ሙሉጌታ አጽብሃ ከመቀሌ ሃብታሙ ስዩም ከዋሽንግተን ዲሲ ያጠናቀሩትን ዘገባ ሃብታሙ ስዩም ያቀርበዋል።