በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጆ ባይደን ዲሞክራቲክ ፓርቲን ወክለው ለፕሬዚዳንትነት እንደሚወዳደሩ ገለፁ


የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን
የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን

የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ዲሞክራቲክ ፓርቲውን ወክሎ ለፕሬዚዳንትነት ለመወዳደር በሚካሄደው የምርጫ ዘመቻ እንደሚስተፉ ዛሬ አስታውቀዋል።

ፕሬዚዳንት ዶናላድ ትረምፕን ለመወዳደር ዘመቻ ከጀመሩት በርካት ዲሞክራቶች መካከል አንደ ሆነዋል።

ነባር የዴላወር ክፍለ ግዛት ሴኔተርና በኦባማ አስተዳደር ወቅት የሁለት የሥራ ጊዜ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት ባይደን ከቬርሞንት ክፍለ ግዛት ሴኔተር በርኒ ሳንደርስና ከሌሎች ተፎካካሪዎች ጋር በዲሞክራስያዊ ፖርቲ ለመሰየም ይወዳደራሉ። ባይደን የሌሎቹ ተፎካካሪዎቻቸውን ያህል ገንዘብ የማሰባሰብ አቅማቸው ምን ያህል እንደሆነ ባይታወቅም በውጭ ፖሊሲ፣ በወንጀል ፍትህና በሀገር ውስጥ ፖሊሲ ያላቸው ተመክሮ ከሌሎቹ ተወዳዳሪዎች የሚደርሳቸው የለም ተብሏል።

ባይደን ዛሬ ማለዳ ባወጡት መግለጫ የዩናይትድ ስቴትስ መሰረታዊ እሴታና በዓለም ደረጃ ያላት ቦታ አደግ ላይ ወድቋል ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG