በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ወደ ግንባር አደረጃጀት ከፍ እንዲል ተወሰነ


ባለፈዉ ሰኔ አስራ ስምንት ሁለት ሺህ ሶስት ዓመተ ምህረት ባካሄደዉ ስብሰባ ላይ ባሳለፈዉ ዉሳኔ መሰረት፣ ለስራ አስፈጻሚ ኮሚቴዉ ወደ ግንባር የሚደረገዉን ሽግግር አጠናክሮ እንዲቀጥል መመሪያ ተሰጥቶት እንደነበር መድረክ ዛሬ ያወጣዉ መግለጫ ያስታዉሳል። ከዚሁ በመነሳት በአባል ድርጅቶች መካከል ለብዙ ወራት ምክክርና ድርድር ሲደረግ መቆየቱንም መግለጫዉ ጨምሮ ጠቅሶአል።
በዚሁም መሰረት የመድረክ አባል የፓለቲካ ፓርቲዎች በዘጠኝ ዋና ዋና ጉዳዮችና ሌሎች ዝርዝር ነጥቦችም ላይ ከስምምነት መድረሳቸዉ ታዉቋል። ከእነዚህም መካከል መለስተኛ የፓለቲካ ፕሮግራም የግንባሩ ፕሮግራም ሆኖ እንዲያገለግል፤ የግንባሩ ድርጅታዊ መዋቅር ለአሰራር ለአፈጻጸም እንዲያመች ማሻሻዎች በማድረግ የጠቅላላ ጉባኤዉን የመሰብሰቢያ ጊዜና የግንባሩን የበላይአመራር አባላት አገልግሎት ዘመን መወሰን የሚሉ ይገኙበታል። የመድረክ አመራር አባል ዶክተር መረራ ጉዲና ወደ ግንባር የሚደረገዉ ሽግግር ለጋራ ትግልና እንቅስቃሴ በእጅጉ እንደሚረዳ በማብራራት ለጋዜጠኞች ጥያቄ መልስ ሰጥተዋል። መግለጫዉን የተከታተለዉ መሃል መለስካቸዉ አመሃ ያላከልንን ዘገባ ያዳምጡ።

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG