በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከመድረክ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ


ኢህአዴግ ኢትዮጵያን ለሰላሳ ዓመታት ለመግዛት እቅድ አለው ይላሉ

ባለፈው ሳምንት ከኢትዮዽያ ም/ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ምኒስቲር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ጋር በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ተመርኩሰን ቃለ-መጠይቅ ማድረጋችን ይታወሳል።ዛሬ ደግሞ የኢትዮዽያ ተቃዋሚዎች በጉዳዩ ላይ አወያይተናል።የመድረክ ምክትል ሊቀ-መንበር እና የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ፕሮፈሰር በየነ ዼጥሮስ እንግዳችን ናቸው።

ፕሮፌሰር በየነ ”ኢህአዴግ አንድ አውራ ፓርቲ በሚል አብዮታዊ ዴሚክራሲ የሚከተል መንግስት በጣም ረዥም ለሆኑ ዓመታት ከሰላሳ ዓመታት በላይ ብቻውን አገሪትዋን ለመግዛት እና ኢትዮዽያ ውስጥ እድገት ለማምጣት እቅድ እንዳለው በፅሑፍም በፖሊሲም የገለፀው ነገር ነው” ይላሉ።

ፕሮፌሰሩ በአንድ ወቅት ከቢቢሲ ጋር ባካሄዱት ቃለ-ምልልስ፣የኢትዮዽያ መንግስት ከውጭ የሚቀበለው እርዳታ ለፖለቲካ ዓላማ ይጠቀምበታል ማለታቸውን በማስታወስ፣የእንግሊዝ ባህር ማዶ ልማት ሃላፊ አንድርው ሚሸል ግን ”ማረጋገጫ ማግኘት አልተቻለም” እንዳሉ ይታወቃል።የእርስዎ መልስ ምንድነው ተብለው ፕሮፌሰር በየነ ሲመልሱ ”አንድሪው ሚሸል ከግንዛቤ ማነስ ወይም ከመረጃ እጦት የተናገሩት ነው።አንድ ባለስልጣን ወደ ሌላ አገር ሲሄድ፣መግለጫ ይሰጠዋል፣በዛ መሰረት የሰማውን መልሶ ማስተጋባት ነው።ስለዚህ የአንድሪው ሚሸል ንግግር እንደዋቢ ቀርቦ የእኛን ውሸት፣የመንግስትን እውነት ለማረጋገጥ እንደምስክር ሆኖ ለመቅረብ ብቃት የለውም” ይላሉ።

XS
SM
MD
LG