የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ባለፈው ቅዳሜ አምስተኛውን ጠቅላላ ጉባዔውን ባካሄደበት ወቅት አገሪቱ እንድትለማ መሠረታዊ የመዋቅር ለውጥ እንዲደረግ ጠይቋል።
በኢትዮጵያ የህግ የበላይነት የለም፣ ታላላቅ ባለሥልጣናት በሙስና ተዘፍቀዋል፣ በተከሰተው የኑሮ ውድነት ድሆች የባሰ ደኅይተዋል የሚሉ ትችቶች በጉባዔው ላይ ተደምጠዋል።
መድረክ በቅዳሜው ጉባዔው በመንግሥት ላይ በሠነዘራቸው ነጥቦች ላይ የኢትዮጵያን መንግሥት መልስ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ለዛሬ አልተሳካም፤ በተነሱት ነጥቦች ላይ ወደፊት የመንግሥትን መልስ ለማቅረብ እንጥራለን።
ዝርዝሩን ያዳምጡ