በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ በኢትዮጵያ የእርዳታ ለጋሾችን ስብስብ ወቀሰ


"በደኃው ኢትዮጵያዊ የዴሞክራሲና ሰብአዊ መብቶች መረገጥ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥትና የለጋሽ አገሮች ቡድን አቋም የተቀራረበ ነው" ሲል የተቃዋሚዎች ጥምረት፣ መድረክ ከሰሰ።

ዓለም አቀፍ የስብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዋች በቅርቡ የኢትዮጵያ መንግሥት ከለጋሾች የሚሰጠውን እርዳታ ለፖለቲካ መጨቆኛ ያውለዋል ሲል ያወጣውን ዝርዝር ሪፖርት የለጋሽ አገሮች ስብስብ የሆነው ዳግ (DAG) መቃወሙ ይታወሳል።

መድረክ ይህን እርምጃ ተቃውሞ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ከቁብ ያለመቆጠሩ አሳዝኖናል ብሏል ።

ዳግ፥ እርዳታ ለፖለቲካ መሣሪያነት እየዋለ ነው የሚለውን ስሞታ ተከትለን ባደረግነው ማጣራት እንደዚያ ያለ ሁኔታ አለመኖሩን አረጋገጠናል የሚል አስተያየት መሠንዘሩን የመድረክ መግለጫ ጠቅሶ የማጣራቱ የመጀመሪያው ምዕራፍ ሥራ በለጋሾችና በኢትዮጵያ መንግሥት መካከል ስምምነት የተደረሰባቸውን የቁጥጥር ዘዴዎች ብቃትና ጥንካሬ በመመዘን የተገደበ የቢሮ ሥራ እንጂ የተባሉትን ክሦች የማጣራት ዓላማ አልነበረውም ብሏል። "ለዴሞክራሲና ለስብአዊ መብቶች ትልቅ ክብር እንሰጣለን" የሚሉት ለጋሽ አገሮች ቅድሚያ ሊሰጡት ይገባ የነበረው ይህ የመብቶች "የዳግ ሪፓርት ዋና ጭንቀት የዴሞክራሲና የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በመፈጸሙ ምክንያት እርዳታው እንዳይቋረጥ በሚል ሽፋን ነገሮችን ተሽቀዳድሞ ማድበስበስ ነው" ብሏል መድረክ በመግለጫዉ። ለዝርዝሩ ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG