በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በምርጫው ላይ የኬንያ ሚድያ የየራሱን ድምር እያወጣ ነው


የምርጫ አስፈፃሚዎች በኪሊሜራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የምርጫ ጣቢያ የድምፅ ቆጠራ እያካሄዱ፤ ናይሮቢ፣ ኬንያ እአአ 8/9/2022
የምርጫ አስፈፃሚዎች በኪሊሜራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የምርጫ ጣቢያ የድምፅ ቆጠራ እያካሄዱ፤ ናይሮቢ፣ ኬንያ እአአ 8/9/2022

የኬንያ መገናኛ ብዙኃን “የፕሬዚዳንታዊ ምርጫውን ድምፅ እየደመሩ መዘገብ እንዲያቆሙ አልተጠየቁም” ሲሉ በመንግሥት የተቋቋመው የሚዲያ ካውንስል ወይም የመገናኛ ብዙኃን መማክርት ጉባዔ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዛሬ አስታወቁ።

ተቀራራቢ በሆነው የምርጫ ውጤት ላይ የሚወጡ ዘገባዎች እየተቀዛቀዘ መምጣታቸው ተነግሯል።

ዋና ሥራ አስፈፃሚው ዴቪክ ኦምዎዮ ለአሶሲየትድ ፕሬስ በሰጡት ቃል “ማንም ማንንም ምንም እንዲያቆም አልጠየቀም” ብለዋል።

ይሁን እንጂ “አኀዞቹ የሚጣጣሙ እንዲሆኑ እንፈልጋለን፤ ቢያስተያዩና ቢያመሳክሯቸው እንመርጣለን” ሲሉም ኦሞዮ አክለው መክረዋል።

ኦሞዮ በዚህ ጉዳይ ከመገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎች ጋር ለመወያየት ወደ ስብሰባ እያመሩ እንደነበረ ተናግረዋል።

ኬንያ በተቃዋሚ መሪው ራይላ ኦዲንጋና በምክትል ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ መካከል እየተካሄደ ባለው ትንቅንቅ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የመለያ ድምፅ ልታስሰጥ እንደምትችልም አሶሲየትድ ፕሬስ ጠቁሟል።

ካውንስሉ ባለፈው ረቡዕ ባወጣው መግለጫ የተለያዩ ውጤቶች መሰማታቸው “እያደገ የመጣ ሥጋት” መፍጠሩን ገልፆ ኬንያዊያን ወጥና ትክከለኛ የሆነ ውጤት ማግኘታቸው የሚረጋገጥበትን አስቸኳይ መፍትኄ ለመሻት ከሚዲያ ባለቤቶችና ኤዲተሮች ጋር እየተመካከረ መሆኑን አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG