በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የልማት ግቦቹ በአፍሪካ እያዘገሙ ነው


የሚሌኒየሙን የልማት ግቦች ለመምታት አፍሪካ ከአሕጉሮቹ ሁሉ ወደኋላ መቅረቷን አንድ ሪፖርት አመለከተ፡፡

ይሁን እንጂ በተለያየ ደረጃም ቢሆን በሁሉም የልማት ግቦች አዎንታዊ እርምጃዎች መታየታቸውን በሁሉም የልማት ግቦች አዎንታዊ እርምጃዎች መታየታቸውን ዘገባው አመልክቷል፡፡

ይህንን የ2010 ዓ.ም የአፍሪካ ሃገሮች ወደሚሌኒየሙ የልማት ግቦች የሚያደርጉትን ግሥጋሴ የቃኘ ዘገባ ያዘጋጁት የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን፣ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ እና የመንግሥታቱ ድርጅት የልማት ፕሮግራም ናቸው፡፡

ዘገባው እአአ በ2010 ዓ.ም አፍሪካ ወደ ሚሌኒየሙ የልማት ግቦች የምታደርገው ግሥጋሴ ምን ደረጃ እንደደረሰ ይቃኛል፡፡

አዲስ አበባ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስብሰባ ማዕከል ይፋ የተደረገው ይኸው ዘገባ እንደሚያመለክተው አፍሪካ ከሌሎቹ አህጉሮች ጋር ስትነፃኀር ወደሚሌኒየሙ የልማት ግቦች በሚደረገው ጉዞ ወደኋላ ቀርታለች፡፡ ብዙ የአፍሪዥከ ሃገት ከአምስት ዓመት በኋላም ቢሆን "አንዳንዶቹን የልማት ግቦች አይመቱ ይሆናል" ሲሉ በአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን የኢኮኖሚ ልማትና የኔፓድ ክፍል ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ኢማኑኤል ንዶዜ ተናግረዋል፡፡

ለዝርዝሩ ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG