በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የማክዶናልድ ኮምፒውተር ሥርዓት ለሰዓታት ተቋረጠ


የማክዶናልድ ምልክት በዊሊንግ፤ ኢል እ/አ/አ መጋቢት 14/2024
የማክዶናልድ ምልክት በዊሊንግ፤ ኢል እ/አ/አ መጋቢት 14/2024

የፈጣን ምግብ አቅራቢው ማክዶናልድ ኮምፒውተር ሥርዓት በመላው ዓለም ለሰዓታት በመቋረጡ፣ የተለመደውን የቁርስ አገልግሎት ያላገኙ ደንበኞች ቅሬታቸውን በማኅበራዊ ሚዲያ ገልፀዋል። የስልክ መተግበሪያውም ከአገልግሎት ውጪ እንደነበር ታውቋል።

ኮባንያው የቴክኖሎጂ ችግር እንደገጠመው ዛሬ በማለዳ አስታውቋል። ለማስተካከል እየሞከረ እንደሆነም ገልጿል።

ችግሩ የተፈጠረው በኮምፒውተር ሥርዓቱ ላይ ጥቃት ስለተፈጸመ እንዳልሆነም መሠረቱን ቺካጎ ያደረገው ኩባንያ አስታውቋል።

በጃፓን የሚገኘው ማክዶናልድ በመላ አገሪቱ የሚገኙ በርካታ ምግብ ቤቶቹ ለጊዜው አገልግሎት እንደማይሰጡ አስታውቆ ነበር።

አንዳንዶቹ የማክዶናልድ ምግብ ቤቶች አገልግሎት መልሰው መጀመራቸው ታውቋል። በባንኮክ፣ ሚላንና ለንደን ደንበኞች ምግባቸውን ማዘዝ መጀመራቸው ተነግሯል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG