በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሚያንማር በመላዋ ሃገሪቱ የሚካሄደው ሰልፍ ቀጥሏል


በሚያንማር በሕግ የተመረጠ የሲቪል መንግሥት በኃይል ከሥልጣን ያስወገደውን ወታደራዊ ኃይል በመቃወም በመላዋ ሃገሪቱ የሚካሄደው ሰልፍ ቀጥሏል
በሚያንማር በሕግ የተመረጠ የሲቪል መንግሥት በኃይል ከሥልጣን ያስወገደውን ወታደራዊ ኃይል በመቃወም በመላዋ ሃገሪቱ የሚካሄደው ሰልፍ ቀጥሏል

በሚያንማር የኢንተርኔት አገልግሎት በተከትታይ ለሁለተኛ ቀን ቢቋረጥም በሕግ የተመረጠ የሲቪል መንግሥት በኃይል ከሥልጣን ያስወገደውን ወታደራዊ ኃይል በመቃወም በመላዋ ሃገሪቱ የተካሄደው ሰልፍ ቀጥሏል።

ከትናንት አንስቶ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች በብዛት ጎዳናዎችን አጨናንቀው ቢታዩም የተቃውሞ ሰልፍ አድራጊዎቹን በያንጎን ከሚገኘው የሃገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ ፊት ለፊት ያለውን መንገድ ከመዝጋት አላገዳቸውም።

በሌላ ተያያዥ ዜና የሮይተርስ ዜና ወኪል እንደዘገበው የተቃውሞ ሰልፈኞቹ በያንጎን እና በደቡባዊቷ የማላውሚኒ ከተማ መካከል ያለውን የባቡር አገልግሎት እንዲቋረጥ አድርገዋል፡፡

ዛሬ ማክሰኞ በያንጎን በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ በደርዘን የሚቆጠሩ የቡድሃ መነኮሳት ጭምር መሳተፋቸው ተዘግቧል።

የሚያንማር ጦር ሠራዊት ከሁለት ሳምንታት በፊት የሃገሪቱን ሲቪል መሪ ኡን ሳን ሱቺ እና ሌሎች የሃገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናትን በቁጥጥር ሥር አውሎ ለአንድ ዓመት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ ካወጀ በኋላ በተቃዋሚዎች እና በፖሊሶች መካከል በየዕለቱ የሚታየው ግጭት እያየለ መጥቷል፡፡

ጦር ሰራዊቱ ለዚህ ዕርምጃው ያቀረበው ምክኒያት ባለፈው ጥቅምት 29/2013 ዓ.ም በሃገሪቱ በተካሄደው እና የኡን ሳን ሱቺብሄራዊ የዲሞክራሲ ሊግ እጅግ ከፍተኛ በሆነ ድምጽ ያሸነፈው ምርጫ ውጤት መጠነ ሰፊ ማጭበርበር ተፈጽሞበታል የሚል ነው። ጦር ሰራዊቱ ያቀረበውን መከራከሪያ የሚያንማር የምርጫ ኮሚሽን ውድቅ አድርጎታል።

XS
SM
MD
LG