በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስትር ጂም ማቲስ ደቡባዊ እስያን እየጎበኙ ነው

ዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስትር ጂም ማቲስ
ዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስትር ጂም ማቲስ

አፍጋኒስታን ውስጥ ላለው ዩናይትድ ስቴትስ መራሹ ጦር፣ ዋይት ኃውስ አዲስ ስትራተጂ ይፋ ካደረገ ወዲህ፣ መከላከያ ሚኒስትር ጂም ማቲስ ለመጀመሪያ ጊዜ ደቡባዊ እስያን እየጎበኙ መሆናቸው ተገለፀ።

አፍጋኒስታን ውስጥ ላለው ዩናይትድ ስቴትስ መራሹ ጦር፣ ዋይት ኃውስ አዲስ ስትራተጂ ይፋ ካደረገ ወዲህ፣ መከላከያ ሚኒስትር ጂም ማቲስ ለመጀመሪያ ጊዜ ደቡባዊ እስያን እየጎበኙ መሆናቸው ተገለፀ።

የመከላከያ ሚኒስትሩ ዛሬ ሰኞ ህንድ ዋና ከተማ ሲደርሱ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ናሬንደራ ሞዲን ጨምሮ ከከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ተገናኘዋል።

ማቲስ በህንዲ ቆይታቸው፤ በኒው ዴልሂ እና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል በፍጥነት እያደገ የመጣውን የመከላከያ ግንኙነት ይበልጥ ያጠናክራሉ ተብሎ ተስፋ ተደርጓል።

በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው አንዱ የትብብር መስክ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ከ16 ዓመታት በኋላም እልባት ያላገኘችለት ከታሊባን ጋር ያለው አጣብቂኝ ሁኔታ ነው።

ኒው ዴልሂ በአፍጋኒስታን ጉዳይ ይበልጥ እንድትንቀሳቀስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ያስተላለፉት መልዕክት፣ ከህንድ ጋር የቦካ ቂም ያላትን ፓኪስታንን እንዳስቆጣ ታውቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG