በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶርያ ለተፈፀመው የኬሚካል መሳርያ ጥቃት የዩናይትድ ስቴትስ እርምጃ

የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስትር ጂም ማቲስ
የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስትር ጂም ማቲስ

የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስትር ጂም ማቲስ አሜሪካ ሶርያ ውስጥ ለተፈፀመው የኬሚካል መሳርያ ጥቃት ወታደራዊ እርምጃ ልትወስድ እንደምትች አመላክተዋል። ማቲስ ይህን ያሉት ባለፈው ቅዳሜ ለተፈፀመው “ትርጉም የለሽ የኬሚካል ጥቃት” ላሉት “ከባድ ዋጋ ይከፈልበታል” ሲሉ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትዊተር ከገለጹ በኋላ ነው።

“በመጀመርያ የሚቀርበው ጥያቄ ሩስያ ሁሉም የሶርያ ኪሜካል መሳርያዎች እንዲነሱ ዋስታና የሰጠች ሀገር ሆና ሳለ አሁንም ኬሜካል መሳራያ ጥቅም የሚውልበት ምክንያት ምንድነው? የሚል ነው በማለት ማቲስ ዛሬ በዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስቴር መስርያ ቤት ከቓታሩ ባለሥልጣን ሼኽ ታሚን ቢን ሐሚድ ዐል-ታኒ ጋር በተገናኙበት ወቅት ተናግረዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ሥለ ጉዳዩ ከወዳጅ ሀገሮች፣ ከሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ሀገሮች ድርጅት ኔቶ አጋሮች እንዲሁም ከታትር ጋር እየተነጋገርን ነው ሲሉ ለጋዜጠኞች ገልፀዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG