በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመቄዶንያ ውሳኔ ሕዝብ

የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስትር ጂም ማቲስ
የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስትር ጂም ማቲስ

መቄዶንያ ውስጥ ሊደረግ የታቀደውን የውሳኔ ሕዝብ "ሩስያ አቅጣጫውን ለማሳት እየሞከረች ነው" በሚል፣ የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስትር ጂም ማቲስ ከሰሱ። የመቄዶንያው ውሳኔ ሕዝብ፣ ሀገሪቱ የኔቶ አባል እንድትሆን ጥርጊያውን የሚያመቻች እንደሆነ ነው የተገለፀው።

መቄዶንያ ውስጥ ሊደረግ የታቀደውን የውሳኔ ሕዝብ "ሩስያ አቅጣጫውን ለማሳት እየሞከረች ነው" በሚል፣ የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስትር ጂም ማቲስ ከሰሱ። የመቄዶንያው ውሳኔ ሕዝብ፣ ሀገሪቱ የኔቶ አባል እንድትሆን ጥርጊያውን የሚያመቻች እንደሆነ ነው የተገለፀው።

ማቲስ፣ አብረዋቸው ወደ መቄዶንያ ለሚጓዙ ጋዜጠኞች በሰጡት ቃል፣ ውሳኔ-ሕዝቡ እንዳይሳካ ለማድረግ ሞስኮ አፍቃሪ ሩስያ ቡድኖችን በገንዘብ እንደምታማልል ምንም ጥርጣሬ እንደሌላቸው አመልክተዋል። ይህም፣ መቄዶንያ የኔቶ አባል እንዳትሆን በተደጋጋሚ ደንቃራ የሆነችውን የግሪክን ፍላጎት የሚያሟላ ይሆናል ብለዋል ማቲስ። መቄዶንያ ለመጪው መስከረም 23 ቀን የታቀደውን ውሳኔ ሕዝብ፣ በራሷና በራሷ ብቻ እንድታካሂደው እንፈልጋለን ሲሉ የዩናይትድ ስቴትሱ መከላከያ ሚንስትር ጂም ማቲስ አሳስበዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG