በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእናቶችን ሞት የሚቀንስ አዲስ ግኝት በኢትዮጵያ


ዶክተር ሓጐስ ጐደፋይ
ዶክተር ሓጐስ ጐደፋይ

ኢትዮጵያ ውስጥ በወሊድ ጊዜ የሚያጋጥመውን የእናቶችን ሞት ለመቀነስ የሚያስችል አዲስ ግኝት ለመጀመርያ ጊዜ በጥናት መገኘቱን ተዘግቧል።

ኢትዮጵያ ውስጥ በወሊድ ጊዜ የሚያጋጥመውን የእናቶችን ሞት ለመቀነስ የሚያስችል አዲስ ግኝት ለመጀመርያ ጊዜ በጥናት መገኘቱን ተዘግቧል።

ጥናቱን ያካሄዱት ዶክተር ሓጐስ ጎደፋይ ይባላሉ፤ ዶክተር ሓጐስ ከታች ወደ ላይ የሚካሄደው የጥናት ዘዴ አዋጭነት እንዳለው አረጋግጠዋል።

ዶክተር ሻጐስ ጎደፋይ የናቶች ሞት ትላንት፣ዛሬና ነገ በተለይም በትግራይ ክልል ውስጥ እየተካሄደ ስላው ልምድና ውጤት አራት የምርምር ውጤቶችን በያዘው መጽሓፋቸው ውስጥ ተካቷል።

የእናቶችን ሞት ለመቀነስ ከላይ የሚመጣውን ስሌት ብቻ መውሰድ ግምታዊ ከመሆናቸው የተነሳ ሊያሳስቱ እንደሚችሉና በአንፃሩ ከታች ከእያንዳንዱ እናት የሚገኘውን መረጃ መጠቀም እውነታውን በይበልጥ እንደሚያስረዳ ዶክተር ሓጐስ ይገልፃሉ። ጥናቱ ላይ ከትግራይ ክልል 6 ወረዳዎች ውስጥ 19 ሽሕ እናቶች ተካቷል።

የእናቶችን ሞት ለመቀነስ ዪሚካሄደው ጥረት ከህክምናዊ ይዘቱ ብቻ ሳይሆን ከማህበራዊ እይታ አንፃርም መጠናት እንዳለበት ምሁሩ ይናገራሉ። ከዚህም በመነሳት በጤና ዙርያ እርስ በርሳቸው እንዲረዳዱ የተደራጁ እናቶች ካልተደራጁት በበለጠ የሞት አደጋ እንደማያጋጥማቸው ጥናቱ ላይ ተረጋግጧል።

በኢትዮጵያ በ1990 የፈረንጆች አቆጣጠር ከ100 ሽሕ እናቶች 1400 በወሊድ ጊዜ ህይወታቸውን ያጡ እንደነበርና ይህም ከአፍሪካ የከፋ ደረጃ ላይ እንደነበረ ጥናቶች ይጠቁማሉ። በሃገሪቱ ከ1990 እስከ 2015 በተካሄደው ጥረት የሞት መጠኑ ወደ 353 ዝቅ እንዲል ተደርጓል። አሁንም ቢሆን እንደ አንድ ትልቅ አደጋ ታይቶ የተቀናጀ ስራ እየተካሄደበት ይገኛል ተብሏል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የእናቶችን ሞት የሚቀንስ አዲስ ግኝት በኢትዮጵያ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:12 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG