በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሊቢያ ሠላሳ ሥድስት አስከሬኖች የተቀበሩበት የጅምላ መቃብር ተገኘ


ሊቢያ ቤንጋዚ ከተማ አቅራቢያ ቢያንስ ሠላሳ ሥድስት አስከሬኖች የተቀበሩበት የጅምላ መቃብር ተገኘ።

ሊቢያ ቤንጋዚ ከተማ አቅራቢያ ቢያንስ ሠላሳ ሥድስት አስከሬኖች የተቀበሩበት የጅምላ መቃብር ተገኘ።

አስከሬኖቻቸው የተገኙት ሰዎች ማንነት አልታወቀም፣ በጥይት የተመቱ ናቸው ተብሏል።

በአንድ ሪፖርት መሰረት አንዳንዶቹ አስከሬኖች ሙሉ የሥራ ልብስ የለበሱ ሌሎች ደግሞ የሥፖርት ቱታ የለበሱም አሉባቸው።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሊቢያ ተወካይ ኻሳን ሳላሜ ባወጡት መግለጫ አረመኒያዊው ወንጀል እንደስቆጣቸው ገልፀው ምርመራ እንዲካሄድ አሳስበዋል።

ሁለቱም የሊቢያ ተቀናቃኝ አስተዳደሮች፣ ዓለምቀፍ ዕውቅና ያለው የትሪፖሊው መንግሥትና በሀገሪቱ ምሥራቃዊ ክፍል በኻሊፋ ሃፍታር የሚመራው መንግሥት ግድያዎቹን አውግዘዋል። ምርመራ እናካሂዳለን ሲሉም ቃል ገብተዋል። የሃፍታር ተዋጊዎች ባላፉት ሦስት ዓመታት የተካሄዱትን በርካታ ግድያዎች በመፈፀም ይጠረጠራሉ ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG