በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዶሚኒካ ዝናብ በቀላቀለ ከባድ አውሎ ነፋስ በ“ማሪያ” ሄሪኬን ተጎዳች


GOES East satellite image provided by NASA taken at 20:30 UTC, shows the eye of Hurricane Maria as it nears Dominica, Sept. 18, 2017.

ዶሚኒካ የተባለችው የካሪብያን ደሴት፤ “ማሪያ” የሚል ቅጽል በተሰጠው ሄሪኬን /ብርቱ ዝናብ የቀላቀለበት ከባድ አውሎ ነፋስ/ ክፉኛ ተጎድታለች።

ዶሚኒካ የተባለችው የካሪብያን ደሴት፤ “ማሪያ” የሚል ቅጽል በተሰጠው ሄሪኬን/ብርቱ ዝናብ የቀላቀለበት ከባድ አውሎ ነፋስ/ ክፉኛ ተጎድታለች።

በደረጃ አምስት የተፈረጀው ሂሬኪን ማርያ ወደ ቨርጂን ደሴቶችና ወደ ፖርቶሪኮ አምርቷል።

እስካሁን ባለው ጊዜ በተገኘው ዜና መሰረት “ሰፊ ጥፋት ደርሷል” ሲሉ የዶሚኒካ ጠቅላይ ሚኒስትር ሩዝቬልት ስከርት በፌስቡክ ገልፀዋል።

“እስካሁን ባለው ጊዜ በገንዘብ ሊገዛና ሊተካ የሚችለውን ነገር ሁሉ አጥተናል። ትልቁ ስጋቴ በቀጠይነት በወረደው ከባድ ዝናብ ምክንያት የመሬት መደርመስ ቢከሰት በሰው ህይወት ላይ ሊያደርሰው የሚችለው ሞትና ጉዳት ነው” ሲሉ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡

ጠቅል ሚኒስትር ስከርት አያይዘውም፣ አሁን ትኩረታችን በፍርስራሾቹ፣ ጉዳት የደረሰባቸውንና መውጫ ያጡትን ሰዎች መፈለግ ነው ብለዋል።

ይህን ለማድረግም ዓለምቀፍ ድጋፍ እናገኛለን የሚል ተስፍ እንዳላቸው ሳይገልጹ አላለፉም። “ማንኛውም አይነት ዕርዳታ ያስፈልገናል” ነው ያሉት።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG