በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የሦስት ቀናት የአፍሪካ ጉብኝት

የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና የቡርኪና ፋሶ ፕሬዚዳንት ሮቸ ማርክ ክርስቲያን ካቦረ
የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና የቡርኪና ፋሶ ፕሬዚዳንት ሮቸ ማርክ ክርስቲያን ካቦረ

የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የሦስት ቀናት የአፍሪካ ጉብኝታቸውን፣ ዛሬ ማስከኞ ከቡርኪና ፋሶ በመጀመር፣ ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሮቸ ማርክ ክርስቲያን ካቦረ ጋርም መገናኘታቸው ተገለፀ።

የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የሦስት ቀናት የአፍሪካ ጉብኝታቸውን፣ ዛሬ ማስከኞ ከቡርኪና ፋሶ በመጀመር፣ ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሮቸ ማርክ ክርስቲያን ካቦረ ጋርም መገናኘታቸው ተገለፀ።

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት የዛሬ ውሎ፣ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪች ንግግር ማድረግንና ኦጋዱጉ ውስጥ ከሚኖሩ የፈረንሳይ ማኅበረሰብ አባላት ጋር መገናኘትን ያካትታል።

የፕሬዚዳንት ማክሮን የአፍሪካ ጉብኝት ዋና ትኩረት ሴኩሬቴ፣ የሥራ ዕድሎች፣ የአየር ንብረትና ፍልሰተኛነት መሆናቸውም ተገልጿል።

ነገ ረቡዕ አይቮሪ ኮስት ውስጥ በሚካሄደው የአውሮፓ ሕብረትና የአፍሪካ ጉባዔ የጋራ ስብሰባ ላይ የአፍሪካ ወጣቶች ጉዳይ ዋና የመወያያ ርዕስ እንደሚሆንም ተገልጿል።

ፕሬዚዳንት ማክሮን የጉዟቸው ማብቂያ በሆነች ጋናም ከወጣቶች ጋር እንደሚገናኙና እንደሚወያዩም ታውቋል።

ማክሮን፣ ጋናን በመጎብኝ የመጀመሪያው የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ይሆናሉ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG