በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጉዞ አድዋ ተጓዦች በደሴ


የአድዋ ድል ስምነተኛ ዙር ተጓዦች
የአድዋ ድል ስምነተኛ ዙር ተጓዦች

በሰሜኑ የኢትዮጵያ አካባቢ የጸጥታ ሥጋት ቢኖርም ጉዟቸውን በስኬት ለማጠናቀቅ መዘጋጀታቸውን የአድዋ ድል ስምነተኛ ዙር ተጓዦች አረጋገጡ፡፡

ተጓዦቹ በአካባቢው ያለውን እውነታ በመረዳት የሰብአዊ ድጋፍ እንዲደርስ የማድረግ ስራዎችን ትኩረት ሰጥተው እንደሚያከናውኑ አስታውቀዋል፡፡

ጎዞውን እስከ ኪሊማንጃሮ በማዝለቅ የአድዋን አፍሪካዊነት የማጠናከር ሥራ ይሰራል ተብሏል፡፡ 125 ተጓዦችን አካተው 125ኛውን የአድዋ የድል በዓል ለመዘከር ጥር 9/2013 ዓ.ም የተነሱት የጉዞ አድዋ ስምንተኛ ዙር የእግር ተጓዦች ደሴ ከተማ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

ጉዞው ከወትሮው በተለየ ዓለማቀፍ የጤና፤ ሃገራዊ የጸጥታ ስጋቶች በሚስተዋሉበትበት ወቅት ነው የሚካሄደው፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

የጉዞ አድዋ ተጓዦች በደሴ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:13 0:00


XS
SM
MD
LG