በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካዊያን ሰልፍ ለፍትህ

አሜሪካዊያን ትዕይንተ-ህዝብ ለፍህ፤ ቅዳሜ - ታኅሣስ 4/2007 ዓ.ም

በዩናይትድ ስቴትስ የፖሊስ ኃይል ፀጥታ የማስጠበቅ አሠራሮችን የሚለውጥ ህግ እንዲወጣ አሜሪካዊያን ቅዳሜ - ታኅሣስ 4/2007 ዓ.ም ትዕይንተ-ህዝብ አካሂደዋል።

please wait

No media source currently available

0:00 0:07:26 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በዩናይትድ ስቴትስ የፖሊስ ኃይል ፀጥታ የማስጠበቅ አሠራሮችን የሚለውጥ ህግ እንዲወጣ አሜሪካዊያን ቅዳሜ - ታኅሣስ 4/2007 ዓ.ም ትዕይንተ-ህዝብ አካሂደዋል።

በቅርቡ የሁለት ጥቁር አሜሪካዊያን ህይወት በእጃቸው ያለፈው የፖሊስ ባልደረቦች ክሥ እንዳይመሠረትባቸው በቅድሚያ ክሥ ምርመራ የሕዝብ ኮሚቴዎች ከተወሰነ ወዲህ በመላ ዩናይትድ ስቴትስ የተቃውሞ ሰልፎች ሲካሄዱ ሰንብተዋል።

ቅዳሜ ኒውዮርክ፣ ቦስተንና ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በተካሄዱ ሰልፎች ላይ በአሥር ሽሆች የተቆጠሩ አሜሪካዊያን ተገኝተዋል።

በፖሊስ ባልደረቦች በቅርብ ጊዜያት ህይወታቸው ያለፈው ጥቁር አሜሪካዊያን ሁኔታ በመላ ሀገሪቱ ህዝባዊ ተቃውሞዎችን ቀስቅሷል።

በአንዳንድ ሥፍራዎች የሁከት ሁኔታዎች ተፈጥረዋል፤ የንብረት ጉዳት ደርሷል፡፡ ከነዚህ ሠልፎች በዓይነቱ ትልቅ የሆነው የቅዳሜው የዋሽንግተን ዲሲ ህዝባዊ ተቃውሞ ሰላማዊ ነበር።

ቅዳሜ ማለዳ ከዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት አቅራቢያ በመነሳት አሜሪካዊያን በታሪካዊው የፔንሲልቫንያ ጎዳና ወደ ህዝብ ተወካዮቹ መቀመጫ ካፒቶል ሂል የእግር ጉዞ አድርገው የተቃውሞና የለውጥ ጥያቄ ድምፅ አሰምተዋል።

“እጆቼን አንስቻለሁ፤ አትተኩስ!” ሲሉ እጃቸውን ወደ ላይ በማንሳት በፈርግሰን ሚዝዩሪ በፖሊስ ባልደረባ በበርካታ ጥይቶች ተደብድቦ ህይወቱ ያለፈው ጥቁር አሜሪካዊ የ18 ዓመት ወጣት ማይክል ብራውንን ሁኔታ ሲቃወሙ፤ “ታፈንኩኝ! መተንፈስ አቃተኝ!” በማለት ደግሞ በኒውዮርክ በፖሊስ ባልደረባ ክንድ አንገቱን ታንቆ ህይወቱ ያለፈው ኤሪክ ጋርነርን አሟሟት አውግዘዋል።

በስፋት ደግሞ፤ በፖሊስ ባልደረቦች፤ በተለይ አነስተኛ ቁጥር ባላቸውና በምጣኔ ኃብት ዕድገት ያልተካተቱ ማኅበረሰቦች ላይ የሚደርሱ የመብቶች ጥሰቶች እንዲቆሙ ጠይቀዋል።

በዚህ ሠልፍ አሜሪካዊያን የቆዳ ቀለም፣ ፆታ፣ ፅድሜና ኃይማኖት ሳይለያያቸው እጅ-ለእጅ ተያይዘው ነው በሠልፉ ላይ የታዩት።

በዚህ ሰላማዊ ሠልፍ የፖሊስ የጭካኔ አድራጎቶች “በግል በራሳችን ወይም በቤተሰቦቻችን አባላት ላይ ተፈፅመዋል” ያሉ እናቶች፣ አባቶች፣ እህቶችና ወንድሞች፤ ከየቤተሰቦቻቸው የተጎዱባቸውን ሰዎቻቸውን ፎቶ ግራፎች ይዘው አደባባይ ወጥተዋል።

ለዝርዝሩ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG