በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኒጀር ላይ የተጣለው የኢኮኖሚ ማዕቀብ ነዋሪዎችን ጎድቷል


 ፎቶ ፋይል፦ የሩዝ ከረጢቶችን ከጭነት መኪና እያወረዱ ኒያሚ ገበያ ኒጀር
ፎቶ ፋይል፦ የሩዝ ከረጢቶችን ከጭነት መኪና እያወረዱ ኒያሚ ገበያ ኒጀር

በምዕራብ አፍሪካዊቷ ኒጀር፣ ከሦስት ወራት በፊት የተካሔደውን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ተከተሎ በተጣለው የኢኮኖሚ ማዕቀብ፣ የኒጀር ነዋሪ ቤተሰቦች፣ ከፍተኛ ችግር ላይ እንደኾኑ ገለጹ፡፡

ምግብ እና ሌሎች ርዳታዎችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች፣ ከደንበር ውጭ ተዘግቶባቸው እንደቆሙ ሲነገር፣ የምግብ ዋጋም በከፍተኛ ንረት እንደጨመረ፣ ነዋሪዎች ለአሶሺዬትድ ፕሬስ ተናግረዋል፡፡

እስከ አሁን ድረስ የቀጠለው ማዕቀብ፣ የሦስት ዓመት የሽግግር ጊዜ በመሠረተው ወታደራዊ መንግሥት ላይ ምንም ተጽእኖ አለማሳደሩ ተመልክቷል፡፡

አንዳንድ የወታደራዊ መንግሥት ደጋፊዎች፣ ማዕቀቡን፥ ሊከፈል የሚገባ ተገቢ መሥዋዕት ነው፤ ብለው እንደሚጠሩት ዘገባው አመልክቷል፡፡

የምግብ ዋጋ ብቻ ሳይኾን፣ እንደ መማሪያ ቁሳቁሶች የመሳሰሉት ሳይቀሩ ዋጋቸው በእጥፍ መጨመሩን፣ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

አጎራባቾቿ በሙሉ ድንበሮቻቸውን የጠረቀሙባት ወደብ አልባዋ ኒጀር፣ በዓለም እጅግ ድኻ ከኾኑ አገሮች አንዷ እንደኾነች ተመልክቷል፡፡

በኢኮኖሚ ማዕቀቡ ሳቢያ፣ አገሪቱ ከውጭ ታገኝ የነበረው የበጀት ድጎማ፣ በ40 ከመቶ ቀንሷል፡፡

እንደ ናይጄሪያ የመሳሰሉ ጎረቤት አገሮች፣ ወደ ኒጀር የሚገባውን የኤሌክትሪክ ኃይል እና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን በማቋረጣቸው፣ በአገሪቱ ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ እንደሚገኝ ተጠቅሷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG