በያዝነው የአውሮፓውያን 2016 ዓ.ም. በ36 የዩናይትድ ስቴትስ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች በንግድና ሥራ ፈጠራ፥ እንዲሁም ሥራ አመራርና ኅዝባዊ አስተዳደር ላይ ባተኮሩ ሦሥት የሥልጠና ፕሮግራሞች ከተለያዩ የአፍሪካ አገሮች የተውጣጡ 1 ሺህ ወጣት መሪዎችን አስተናግደዋል።
ሥልጠናው “ማንዴላ ዋሽንግተን የወጣት አፍሪቃውያን መሪዎች” በመባል የሚታወቀው ትምህርታዊ ፕሮግራም አካል ነው። ፕሮግራሙ በተጨማሪም ከፍተኛ ብቃት ላሳዩ ከሰሃራ በስተደቡብ የሚገኙ የአፍሪቃ ሃገራት ወጣት መሪዎች በተለያዩ የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ የትምሕርት ተቋማት በመዘዋወር ልዩ-ልዩ ክሕሎቶችን ቀስመው ወደየሃገሮቻቸው እንዲመለሱ ለማገዝ የተነደፈ ነው።