በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትረምፕ የምርጫ ዘመቻ አስተባባሪ የነበሩት ፖል ማንፎርት

ፖል ማንፎርት
ፖል ማንፎርት

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የምርጫ ዘመቻ አስተባባሪ የነበሩት ፖል ማንፎርት በወንጀል ክስ ሂደት ላይ ባሉበት በአሁኑ ወቅት ምስክር ሊሆኑ የሚችሉ ሰዎችን ለማነጋገር ተደጋጋሚ ጥረት አድርገዋል ሲሉ ለዩናይትድ ስቴትስ ልዩ ካውንስል ሮበርት ሙለር የሚሰሩ አቃብያነ-ህግ ተናግረዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የምርጫ ዘመቻ አስተባባሪ የነበሩት ፖል ማንፎርት በወንጀል ክስ ሂደት ላይ ባሉበት በአሁኑ ወቅት ምስክር ሊሆኑ የሚችሉ ሰዎችን ለማነጋገር ተደጋጋሚ ጥረት አድርገዋል ሲሉ ለዩናይትድ ስቴትስ ልዩ ካውንስል ሮበርት ሙለር የሚሰሩ አቃብያነ-ህግ ተናግረዋል።

አቃብያነ-ህጉ ትናንት ፍርድ ቤት ላይ ባሰሙት ንግግር ማንፎርትና አንድ ተባባርያቸው በሚሰጡት የምስክርነት ቃል ላይ ተፅዕኖ ለማሳደር ሲሉ ሁለት ምስክሮችን በተደጋጋሚ አነጋግረዋል የሚል ክስ አቅርበዋል።

ማንፎርት ምስክሮቹን ባለፈው የካቲት ወር ያነጋገሩት አዲስ ክስ በተመሰረተባቸውና በቁም እሥር ባሉበት ወቅት ነው።

ሮበርት ሙለር ካች አምና በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በትረምፕ የምርጫ ዘመቻና በሩስያ ጣልቃ ገብነት መካከል ግንኙነት ይኖር እንደሆነ ለማጣራት ምርመራ እያካሄዱ መሆናቸው የሚታወቅ ነው። ማንፎርት በምስክሮች ላይ ተፅዕኖ ለማሳደር አደረጉ የተባለው ሙከራ ሊያሳስራቸው እንደሚችል ተገልጿል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG