በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ካናዳ አንድ አጥቂ ተኩስ ከፍቶ ሁለት ሰዎች ሞቱ


ካናዳ ቶሮንቶ ከተማ ትናንት ማታ አንድ አጥቂ በያዘው ሽጉጥ ተኩስ ከፍቶ ከመታቸው አሥራ አራት ሰዎች ሁለቱ ሞቱ።

ካናዳ ቶሮንቶ ከተማ ትናንት ማታ አንድ አጥቂ በያዘው ሽጉጥ ተኩስ ከፍቶ ከመታቸው አሥራ አራት ሰዎች መካከል ሁለቱ ሲሞቱ ተጠርጣሪው ራሱም ሞቷል።

በቶሮንቶ ግሪክታውን በሚባለው ሰፈር መንገድ ላያ ስንዘዋወር ቢያንስ ሃያ ወይም ሰላሳ የሚሆን የተኩስ ድምጽ ሰምተናል ሲሉ እማኞች ገልፀዋል።

ከተጠርጣሪው ጋር የተኩስ ልውውጥ መካሂዱን የከተማዋ የፖሊስ አዛዥ ማርክ ሶንደርስ ገልፀዋል።

መርማሪዎች የጥቃቱን ምክንያት ለማወቅ ምርመራ ላይ መሆናቸውንም አመልክተዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG