በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የማሊን የሽግግር ፕሬዚዳንት ለመግደል በመሞከር የተወነጀለው መሞቱ ተገለጸ


ፎቶ ፋይል፦ የማሊን የሽግግር ፕሬዚደንት አሲሚ ጎይታን በስለት ወግቶ ለመግደል በመሞከር ተወንጅሎ የተያዘው ግለሰብ ህይወቱ አለፈ
ፎቶ ፋይል፦ የማሊን የሽግግር ፕሬዚደንት አሲሚ ጎይታን በስለት ወግቶ ለመግደል በመሞከር ተወንጅሎ የተያዘው ግለሰብ ህይወቱ አለፈ

የማሊን የሽግግር ፕሬዚደንት አሲሚ ጎይታን በስለት ወግቶ ለመግደል በመሞከር ተወንጅሎ የተያዘው ግለሰብ በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር በነበረበት ባለፈው ሳምንት ሆስፒታል ገብቶ በነበረበት ሆስፒታል ህይወቱ ማለፉን የሀገሪቱ መንግሥት ትናንት አስታወቀ።

ባለፈው የአንድ ዓመት ጊዜ ሁለት የመንግሥት ግልበጣዎችን ያቀነባበሩት የልዩ ኃይሎች ኮሎኔሉ ጎይታ ባለፈው ማክሰኞ ባማኮ በሚገኝ መስጂድ ጸሎት ላይ ሳሉ አጥቂው በስለት ሊወጋቸው ሞክሮ ምንም ጉዳት ስይደርስባቸው አምልጠዋል።

ኮሎኔል ጎይታን የጸጥታ ኃይሎች አጅበው ሲያወጧቸው በሌላ በኩል ወታደሮች አንድ ሰው ይዘው መኪና ውስጥ ሲያስገቡ የሚያሳይ ቪዲዮ ማግኘቱን ሮይተርስ ዘግቦ ነበር።

ትናንት የወጣው የመንግሥቱ መግለጫ "ሰውየው እየተመረመረ እያለ የጤናው ሁኔታ እያሽቆለቆለ በመሄዱ ወደሆስፒታል ቢወሰድም ህይወቱ አለፈ" ብሏል።

የተጠርጣሪው ህልፈት ምክንያት ምን እንደሆነ ምርመራ እየተደረገ መሆኑ ተዘግቧል።

ከአስር ዓመት በላይ በፈረንሳይ ድጋፍ ከአልቃይዳ እና ራሱን እስላማዊ መንግሥት ብሎ ከሚጠራው ቡድን ጋር የተባበሩ ታጣቂዎችን ስትወጋ የቆየችው ማሊ ባለፈው ዓመት በኮሎኔል ጎይታ የተመራ መፈንቅለ መንግሥት ፕሬዚዳንቱን ኢብራሂም ቡባካር ኬይታን ከገለበጠ ወዲህ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ተዘፍቃለች

ኮሎኔሉ የሽግግር መሪው የነበሩት ባህ ንዳው ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ የሽግግሩ ፕሬዚዳንት ባለፈው ግንቦት ከሥልጣናቸው ተወግደዋል።

XS
SM
MD
LG