በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአውሮፓ ሕብረት ሀገሮችና የአፍሪቃ መሪዎች በስደተኞች ቀውስ መፍትሄ ለማግኘት ተሰብስበዋል


የአውሮፓ ህብረት ሀገሮችና ያፍሪካ መሪዎች ለወቅቱ ያውሮፓ የፍልሰተኞች ቀውስ መፍትሄ ለማግኘት ቫሌታ (Valletta) በምትባል የማልታ ከተማ ተሰብስበዋል።

የአውሮፓ ሕብረት ሀገሮችና ያአፍሪቃ መሪዎች ለወቅቱ ያውሮፓ የፍልሰተኞች ቀውስ መፍትሄ ለማግኘት ቫሌታ (Valletta) በምትባል የማልታ ከተማ ተሰብስበዋል።

በማልታው ጉባዔ ላይ ከተገኙ ያፍሪካ መሪዎች መካከል የሱማልያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዖማር አብዲራስሂድ ሻርማርኬ (Omar Abdirashid Sharmarke) አንዱ ናቸው።

ከቪኦኤ የሱማልኛው ቋንቋ አገልግሎት ጋር አጭር ቃለ ምልልስ አድርገዋል። ሻርማርኬ (Sharmarke) ጉባዔው ላይ ሊነሱ ስለሚችሉ ጉዳዮች እንዲህ ነበር ያሉት።

የአውሮፓ ሕብረት ሀገሮችና የአፍሪቃ መሪዎች በስደተኞች ቀውስ መፍትሄ ለማግኘት ተሰብስበዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:39 0:00

“ለፍልሰት የሚያበቁ ዋነኛ ምክንያቶች ላይ እንነጋገራለን። ስለ ጦርነት፥ ስለ ግጭቶችና ስለ ድህነት እንወያያለን። የፍልሰተኞችን ሕይወት ማትረፍ ስለምንችልበትና ስለ ሕገ-ወጥና ሕጋዊ ስደተኞች ጉዳይም እንነጋገራለን። እንደ እውነቱ ከሆነማ ትክክለኛው ለፍልሰት የሚያበቁ ሁኔታዎች በሚገባ ይታወቃሉ። አንዱ ጦርነት ሲሆን ሌላው ድህነት ነው። ወጣቶች በሃገራቸው የተሻለ ምርጫ የማጣታቸው ጉዳይ ሌላው ነው። በየሃገሮቹ የሚታዩ የመልካም አስተዳደር እጦት እና የሙስና መንሰራፋትም ለፍልሰት ከሚያበቁ ጉዳዮች ውስጥ ይጠቀሳሉ። ጉዳዮቹ በደንብ የታወቁ ቢሆኑም በማልታው ጉባዔ ላይ ያፍሪካና ያውሮፓ መሪዎች ችግሮቹን ጥርት አርገው ለመወያየት እድል ያገኛሉ ብዬ አስባለሁ”ብለዋል።

ያውሮፓ ሕብረት መሪዎች ካፍሪካ አቻዎፓተው ጋር ዛሬ ማልታ ሲገናኙ፥ ቃል ሊገቡ የሚችሉት የገንዘብና ሌሎች እርዳታዎች፥ አደገኛውን የሜዲተራንያን ባህር እያቃረጡ የሚጎርፉትን የዓለም ድሃ ሀገሮች ፍልሰተኞች ቁጥር ይቀንሳል ብለው ተስፋ ያደርጋሉ። ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

የአውሮፓ ሕብረት ሀገሮችና ያአፍሪቃ መሪዎች በስደተኞች ቀውስ መፍትሄ ለማግኘት ተሰብስበዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:32 0:00

XS
SM
MD
LG