በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የምዕራብ አፍሪካ መሪዎች ማሊን ከኤኮዋስ አባልነት አገዷት


የምዕራብ አፍሪካ መሪዎች ማሊን ባለፈው ሳምንት በተካሄደው መፈንቅለ መንግሥት ምክንያት ከልላዊው ማኅበራቸው ከኤኮዋስ አግደዋታል።

የምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማኅበረሰብ አባል ሃገሮች ርዕሳነ ብሄራት ትናንት ዕሁድ ባካሄዱ አስቸኳይ ስብስባ ማሊ ከማኅበሩ እንድትታገድ ወስነዋል። መሪዎቹ በተጨማሪም በሚመጣው የካቲት ወር ምርጫዎች እስከምታካሂድ ሃገሪቱን የሚያስተዳድር አዲስ ሲቪላዊ የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም ጠይቀዋል። የማሊ የፖለቲካ ቀውስ የቀጣናውን ጸጥታ ይብሱን ያደፈርሰዋል ሲሉ አሳሳበዋል።

ባለፈው ሳምንት የሽግግር መንግሥቱን ፕሬዚደንት እና ጠቅላይ ሚኒስትር የገለበጧቸው የቀደመው ባለፈው ነሃሴው ወር የተካሄደውን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት የመሩት ኮሎኔል አሲሚ ጎይታ ናቸው። በቁም እስር ላይ የሚገኙት የቀደሙት የሽግግር ፕሬዚደንት ባህ ኒዳው እና ጠቅላይ ሚኒስትር ሞክታር ኡዋኔ ባስቸኩዋይ እንዲለቀቁ ጠይቀዋል።

XS
SM
MD
LG