በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማሊ በሥልጣን ሽግግር ጉዳይ ንግግር ሊጀመር ነው


በማሊ ከሁለት ሳምንት በፊት የመንግሥት ሥልጣን የተቆጣጠረው ወታደራዊ ቡድን በመጪዎቹ ቅዳሜና ዕሁድ በሥልጣን ሽግግር ጉዳይ ንግግር እንደሚጀምር አስታወቀ።

ድርድሩን ከፖለቲካ ፓርቲዎች ከህዝባዊ ድርጅቶች እና ፕሬዚዳንቱ ኢብራሂም ቡባካር ኬይታ ከሥልጣን እንዲወርዱ የገፋውን ተቃውሞ የመራው የጁን ፊፍዝ እንቅስቃሴ ከተባለው ቡድን ጋር እንደሚያካሂድ ነው ያስታወቀው።

ነገ ቅዳሜ እና ዕሁድ የሚካሄደው ንግግር የሽግግሩን አቅጣጫ የሚተልም ይሆናል ሲል አንድ የወታደራዊው ደርግ ቃል አቀባይ ገልጿል።

የወታደራዊው ደርግ ከሦስት ዓመት በኋላ ሥልጣን ለሽግግር መንግሥት እናስረክባለን ብሎ ነበርየምዕራብ አፍሪካ ሃገሮች የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ አይሆንም አሁኑ ሥልጣን ለሲቪላዊ አስተዳደር አስረክቡ፤ ከአንድ ዓመት በኋላ ምርጫ መካሄድ አለበት ሲል አስታውቋዋቸል።

XS
SM
MD
LG