ዋሺንግተን ዲሲ —
ከፕሬዘዳንቱ ከኢብራሂም ቡባካር ኬይታ ፅ/ቤት የወጣ መግለጫ፣ “ፕሬዘዳንቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩና መላ ካቢኔያቸው ያቀረቡትን የሥራ መልቀቂያ ጥያቄ ተቀብሏል” ይላል።
የሱሜሉ መንግሥት ይህን ዕርምጃ የወሰደው ባለፈው ወር 160 የፉላኒ ከብት አርቢዎች በተጠርጣሪ የዶጋን አዳኞች መገደላቸውን ጨምሮ በሀገሪቱ ማዕከላዊ ግዛት ሁከት መከሰቱን ተከትሎ ነው።
በተባበሩት መንግሥታት ዘገባ መሠረት ባለፈው ዓመት በፉላኒ እና በዶጋን ማኅበረሰቦች መካከል በተካሄዱ ግጭቶች ምክንያት 600 የሚሆኑ ሴቶች፣ ሕፃናትና ወንዶች ተገድለዋል።
ዜጎች መንግሥት ሁከቱን ለማስቆም አልቻለም ሲሉ ከሁለት ሣምንታት በፊት በዋና ከተማዋ ባማኮ ግዙፍ የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄዳቸው ይታወሳል።
ማሊ እአአ በ2012 ባማኮ ውስጥ ለአጭር ጊዜ የቆየውን ወታደራዊ የመንግሥት ግልበጣ ተከትሎ ሙስሊም ፅንፈኞች አብዛኛውን ሰሜናዊ ግዛት ከተቆጣጠሩ ወዲህ፣ ሃገሪቱን ለማረጋጋት እየጣረች ነው፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ