በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በማዕካላዊ ማሊ የተፈፀመው ጥቃት በዘር ላይ የተመሰረተ ነው ተባለ


ባለፈው ዕሁድ በማዕካላዊ ማሊ በሚገኝ መንደር ላይ በተፈፀመ ቢያንስ 35 ሰዎች የተገደሉበት ጥቃት በዘር ላይ የተመሰረተ ነው ተብሏል። ነገር ግን እስላማዊ አማፅያን የሀገሪቱ ክፍሎችንና የድንበሩን አከባቢ የሚቆጣጠሩ በመሆናቸው የዘር ግጭትንና የጂሐድ አሸባሪነትን ለመለያት አስቸጋሪ መሆኑ ተገልጿል።

በግብርና ላይ ይተመሰረቱት ዶጎን የተባለው ጎሳ አባልትና ከፊል አርብቶ አደሮች የሆኑት ፉላኒ ለምዕተ ዓመታት ያህል አብረው በሰላም የኖሩ ቢሆንም አሁን በመካከላቸው የሚካሄደው ግጭት ተባብሷል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለፈው ወር ባወጣው ዘገባ መሰረት በምዕከላዊ ማሊ ባሉት ሁለቱ ጎሳዎች መካከል የሚካሄደው ግጭት የተባባሰው ጽንፈኛ ቡድኖች ስላሉ ነው።

በፊትም ግጭቶች የነበሩ ቢሆን ይህን ያክል አደገኛ አልነበሩም ሲሉ ዳካር ያለው አፍሪካ ጆም የተባለ የጥናትን ምርምር ማዕካል ሥራ አስኪያጅ አሊኒ ቲን አስገንዝበዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG