በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በማዕከላዊ ማሊ በተፈፀመ ጥቃት ቢያንስ 95 ሰዎች ተገደሉ


ዛሬ በማዕከላዊ ማሊ በተፈፀመ ጥቃት ቢያንስ 95 ሰዎች እንደተገደሉ ታውቋል። የታጠቁ ሰዎች ሌሊት በህዝብ ላይ ተኩስ ከፍተው መኖርያ ቤቶችን በእሳት አጋይተዋል።

ጥቃቱ ዒላማ ያደረገው ሶባንቱ የተባለውን መንደር መሆኑን አንድ በቀጠናው ያለ ጋዜጠኛ በአሜሪካ ድምፅ ላለው የፈረንሳኛ አገልግሎት ገልጿል። የሞቱት ሰዎች ብዛት ከ 100 በላይ ሊሆን እንደሚችል ጋዜጠኛው ጠቁሟል።

መንደሩ ዶጎን የተባሉ ብሄረሰቦች የሚኖሩበት ሲሆን በፉላኑ አማፅያን የተከፈተ ሊሆን ይችላል የሚሉ ዘገባዎች ቀርበው ነበር። በዶጎን አርሶ አድሮችና በፉላኒ አርብቶ አደሮች መካከል ለዓመታት ያህል የዘለቀ ውጥረት መኖሩ ታውቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG