ዋሽንግተን ዲሲ —
የማሊ ፕረዚዳንት ኢብርሂም ቦባካር ኬይታ በሳምንቱ ማብቂያ ላይ 4 ሰዎች መንገዶች ላይ በተደረገው የተቃውሞ ስልፍ ከተገደሉ በሁዋላ የሀገሪቱን ህገ-መንግስታዊ ፍርድ ቤት አፍርሰዋል።
ከይታ የምዕራብ አፍሪቃ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ECOWAS ባቀርበው ምክረ-ሃሳብ መሰረት ባለፈው መጋቢት ወር በተካሄደው ምርጫ አጨቃጫቂ የሆኑትን አስመልክቶ የማጣርያ ምርጫ እንዲካሄድ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
የተቃውሞ መሪዎች ግን የተወሰደው እርምጃ በቂ አይደልም በማለት ፕረዚዳንቱ ከስልጣን እስከሚወርዱበት ጊዜ ድረስ ተቃውሞ ማካሄዱን አናቆምም ብለዋል።