በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመድ እና የፈረንሳይ ኃይሎች ከማሊ እንደለቀቁ አገሪቱ ቀውስ ውስጥ ገብታለች


የማሊ ካርታ
የማሊ ካርታ

የተመድ እና የፈረንሳይ ኃይሎች ማሊን ለቀው እንደወጡ፣ ከአልቃይዳ ጋራ ግንኙነት ያላቸው ነውጠኞች ጥቃታቸው እንደጨመረና አገሪቱ አስከፊ ቀውስ ውስጥ እየገባች እንደኾነ፣ በመነገር ላይ ነው።

የሩሲያው ቫግነር ቡድን፣ አገሪቱን የተቆጣጠረውን ሁንታ ለመደገፍ አንድ ሺሕ ወታደሮችን ቢያሰማራም፣ የጸጥታ ክፍተቱን ለመሸፈን አልቻለም።

የእስልምና አስተምህሮ ማዕከል ተደርጋ የምትታየው ቲምቡክቱ፣ ካለፈው ነሐሴ ወር ጀምሮ በከበባ ውስጥ ስትኾን፣ የየብስ፣ የአየር እና የባሕር መጓጓዣዎች እንደተዘጉ ናቸው።

ነውጠኞቹ፣ ቲምቡክቱን በከባድ መሣሪያ እየደበደቡ ናቸው፡፡ በጥቃቱ፣ ከሳምንት በፊት አንድ ሆስፒታል በሮኬት ሲመታ፣ ሁለት ሕፃናት ሕይወታቸውን አጥተዋል።

ከዐሥር ዓመታት በፊት የትዋረግ ዐመፅ በጂሃዲስቶች ተጠልፎ፣ ቲምቡክቱን ከተቆጣጠሩ በኋላ ወደ ደቡብ በማምራት መዲናዋን ባማኮን ሊይዙ ሲሉ፣ በፈረንሳይ እና በተመድ ኃይል እንዲገቱ ተደርገዋል።

ሁንታው፣ 13ሺሕ የተመድ ሰላም አስከባሪዎች እና የፈረንሳይ ወታደሮች፣ ማሊን ለቀው እንዲወጡ ከአደረገ በኋላ፣ አገሪቱን ከነውጠኞቹ የሚታደግ ኃይል እንደሌለ ተነግሯል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG