በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአማጺያን ጥቃት የደረሰባት ማሊ መዲናዋን መቆጣጠሯን አስታወቀች


ባማኮ፣ ማሊ
ባማኮ፣ ማሊ

ማሊ ዛሬ ንጋት ላይ አማጺያን በፖሊስ ማሰልጠኛና ሌሎችም ሥፍራዎች ላይ ያደረሱትን ጥቃትና የተኩስ እሩምታ ተከትሉ፣ መዲናዋን ባማኮ በቁጥጥር ስር ማድረጉን መንግስት አስታውቋል።

“ንጋት ላይ የሽብር ቡድኖች ፋላዴ የፖሊስ ማሰልጠኛን ሊቆጣጠሩ ሞክረው ነበር” ያለው ሰራዊቱ፤ አያይዞም፣ “በአሁን ሰዓት የተቀሩትን የማጽዳት ስራ እየተካሄደ ነው” ሲል በመግለጫው አስታውቋል፡፡ ይፋዊ ተጨማሪ መግለጫ እስኪሰጥ ድረስም ነዋሪዎች ከአካባቢው እንዲርቁ ጥሪ ተደርጓል፡፡

የማሊ ወታደራዊ መንግስት፣ የፖሊስ ማሰልጠኛውን ጨምሮ “በዋና ከተማዋ ያሉ አንዳንድ ቁልፍ ስፍራዎች” ጥቃት ተከፍቶባቸዋል ሲል አስታውቋል።

አንዳንድ ነዋሪዎች ከአየር ጣቢያው አቅጣጫ በኩል የተኩስ ድምጽ ይሰማ ነበር ሲሉ፣ ሌሎች ደግሞ የተኩስ ድምጹ የመጣው ከፖሊስ ማሰልጠኛው አቅጣጫ እንደሆነ ተናግረዋል።

በሌሎችም በርካታ መንደሮች የመሣሪያ ድምጾች መስማታቸውን የገለጹ ሲሆን፤ አንድ የደህንነት ቢሮ ምንጭ ደግሞ፣ አየር ማረፊያው ተዝግቷል ብለዋል፡፡ የፖሊስ ማሰልጠኛው በአየር ጣቢያው አካባቢ የሚገኝ ነው፡፡

ማሊ ከጎርጎሪሳውያን 2012 አንስቶ እስላማዊ አማጺያንን ከሚፋለሙት የምዕራብ አፍሪካ ሃገራት አንዷ ሆናለች፡፡

የፀጥታና ደህንነት ስጋት መፈጠሩ ከአራት ዓመታት በፊት ለተከሰቱት ሁለት ተከታታይ መፈንቅለ መንግስታት ምክንያት እንደሆነ ይነገራል። ማሊን ተከትሉም በጎረቤት ቡርኪና ፋሶና ኒዤር መፍንቅለ መንግስት መካሄዱ ይታወሳል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG