ዋሺንግተን ዲሲ —
በምርጫ የተወዳደሩት የማሊ ፕሬዚዳንት ኖውበከር ኬታ በማጣርያው ምርጫ በከፍተኝ ድምፅ አሸንፈዋል።
በጂሐዳውያን ሚሊሻዎች የግጭት ዛቻ ምክንያት ለማጠርያው ምርጫ ድምፅ ለመስጠት የወጡት ሰዎች ቁጥር 34 ከመቶ ብቻ ነው።
ዛሬ ይፋ የተደረገው ኦፊሴላዊ ውጤት ባለፈው ዕሁድ በተካሄደው የማጣርያ ምርጫ ኬታ የተቃውሞ መሪሶውማይላ ሲሴን በክፍተኛ ድምፅ ማሽነፋቸውን ያሳያል።
መንግሥት በማጣርያው ምርጫ ወቅት ተመድበው በነበሩት 30ሺህ ወታደሮች ላይ 6,000 በመጨመር ከፍተኛ የፀጥታ ጥበቃ ያደረገ ቢሆንም በሰሜን ቲምባክቱ ክልል አንድ የምርጫ ጣብያ ፕሬዚዳንት ተገድለዋል። የምርጫ ጣብያውም በእሳት ጋይቷል።
የመጀመርያው የምርጫ ሂደትም በግጭት ታምሶ እንደነበርና በመቶዎች የሚቆጠሩ የምርጫ ጣብያዎች በዘር ግጭት ምክንያት እንደተዘጉ ተዘግቧል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ