በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የማሊ ፕሬዚዳንት ከሥልጣን መነሳት


የማሊ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ቡባካር ኪታ
የማሊ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ቡባካር ኪታ

የማሊ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ቡባካር ኪታ ትናንት ማክሰኞ ሥልጣናቸውን ለቀቁ። ፕሬዚዳንቱ ሥልጣናቸውን የለቀቁት ያመጹ ወታደሮች በቁጥጥር ሥር ካዋሏቸው ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ነው። በሀገሪቱ ለወራት ግዙፍ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ከቀጠለ በኋላ ትናንት ወታደሮቹ አምፀው ወጥተዋል።

የሰባ አምስት ዓመቱ ቡባካር ኬታ በመንግሥቱ ቴሌቭዥን ቀርበው ባደረጉት ሥስልጣን መልቀቂያ ንግግራቸው ደም እንዳይፋሰስ መከላከል ቢቻል በወደድኩ ነበር ሲሉ ተደምጠዋል።

ፕሬዚዳንቱና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቡቡ ሲሴ ትናንት በፕሬዚዳንቱ መኖሪያ ቤት ከተያዙ በኋላ በአቅራቢያው ባለችው ኬታ ከተማ ወደሚገኘው የጦር ሰፈር ተወስደዋል።

የምዕራብ አፍሪካ ሃገሮች የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ ኤኮዋስ የፕሬዚዳንቱን መታሰር ዜና ተከትሎ አባል ሃገራቱና ማሊን የሚያዋስኑ ድንበሮችን ዘግቷል። አባል ሃገሮቹ የገንዘብ ነክ ግንኙነት እንዳያደርጉም ወስኗል። ማሊን ከድርጅቱ ውሳኔ ሰጭ አካላት አግዷታል።

XS
SM
MD
LG