በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የማሊ ፖለቲካ


የማሊ ዋናው ተቃዋሚ ፓርቲ የፖለቲካ ቀውሱን ለማርገብ በክልሉ መንግሥታት ሸምጋዮች የቀረበውን ዕቅድ ሳይቀበለው ቀርቷል። አስቀድሞም በአክራሪ እስልማና ቡድኖች አመጽ እየታመሰች ባለችው ሃገር አሁን ደግሞ በፖለቲካ ቀውስ ተወጥራለች።

የምዕራብ አፍሪካ መንግሥታት የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ ኤኮዋስ ያቀረበውን ዕቅድ ሰኔ አምስት ንቅናቄ የተባለው ተቃዋሚ ቡድን ውድቅ አድርጓል።

ሸምጋዮቹ ያቀረቡት ዕቅድ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ቡባካር ኪይታ ከተቃዋሚው ፓርቲ ጋር የአንድነት መንግሥት እንዲያቋቁሙ የሚጠይቅ ሲሆን ፕሬዚዳንቱ ሥልጣን እንዲለቁ የሚጠይቀው ተቃዋሚ ፓርቲው እምቢ ብሏል። ፕሬዚዳንቱ ይውረዱ የሚለውን ጥያቄ ኤኮዋስ አልተቀበለም።

XS
SM
MD
LG