በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በማሊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ታገደ


ፎቶ ፋይል፦ ባማኮ፣ ማሊ
ፎቶ ፋይል፦ ባማኮ፣ ማሊ

በማሊ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ሌላ ማሳሰቢያ እስከሚሰጥ ድረስ መታገዱን ሃገሪቱን በመምራት ላይ ያለው ሁንታ ትናንት ረቡዕ አስታውቋል።

ምርጫ ላልተወሰነ ግዜ መታገዱን ባለፈው ዓመት ያስታወቀው ሁንታው፣ የትናንቱ ውሳኔ ደግሞ በሕዝቡ ዘንድ ሥርዓትና ደንብ እንዲሰፍን ለማድረግ ታስቦ የተላለፈ መሆኑን አስታውቋል።

ሃገሪቱ የኢድ አል ፈጥርን በዓል በማክበር ላይ በነበረችበት በትናንትናው ዕለት፣ የሁንታው ቃል አቀባይ አብዱላዬ ማይጋ ማምሻውን በብሔራዊው ቴሌቪዥን ቀርበው መግለጫውን አሰምተዋል።

ባለፉት አራት ዓመታት ሁለት መፈንቅለ መንግሥቶችን የተካሄደባት ማሊ፣ ባልተረጋጋ ፖለቲካ ውስጥ ናት። ከአል ቃይዳ እና እስላማዊ መንግሥት ጋራ ግንኙነት ባላቸውን ጅሃድ ቡድኖች እየተባባሰ የመጣውን የአማፅያን ስብስብ ለአስር ዓመታት ስትታገል ቆይታለች።

በኮሎኔል አሲሚ ጎይታ የተመራው ሁንታ፣ በሃገሪቱ ዲሞክራሲን እንደሚያሰፍን እና ምርጫም ባለፈው የካቲት እንደሚያደርግ ቃል ገብቶ የነበረ ቢሆንም፣ “ቴክኒካዊ ዝግጅት ያስፈልጋል” በሚል ምርጫውን ላልተወሰነ ግዜ አስተላልፏል።

የፈረንሣይ ወታደሮችን ልፀጥታ ጥበቃዋ ትገለገል በነበረችው ማሊ፣ ሁንታው ፈረንሣዮቹን ከሃገሪቱ እንዲወጡ በማድረግ የሩሲያ ቡድኖችን ጋብዟል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG