በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በማሊው የወርቅ ማዕድን አደጋ የሟቾች ቁጥር ከ70 በላይ አሻቀበ


ፎቶ ፋይል፦ በባማኮ፣ ማሊ
ፎቶ ፋይል፦ በባማኮ፣ ማሊ

ባለፈው ሳምንት ማሊ ውስጥ በአንድ የወርቅ ማዕድን ማውጫ የሚገኝ መተላለፊያ ዋሻ መደርመሱን ተከትሎ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ70 በላይ ማሻቀቡ ሲገለጽ፤ የአካባቢው ምንጮች ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደተናገሩት፣ በማዕድን ቁፋሮ ወቅት ለሚከሰቱ አደጋዎች ተጋላጭ በሆነው ክልል የደረሰ አዲስ አደጋ መሆኑ ነው።

የማሊ የማዕድን ሚኒስቴር ባለፈው ማክሰኞ ባወጣው መግለጫ፣ በርካታ የማዕድን አውጪዎች በአደጋው መሞታቸውን ቢያስታውቅም፣ የሟቾችን ትክክለኛ አሃዝ ግን እስካሁን ይፋ አላደረገም።

የፖለቲካ አለመረጋጋት አገሪቱን ለዓመታት ሲያምስ ቢቆይም፣ በማሊ የማዕድን ዘርፍ የበላይነቱን የያዙት የካናዳዎቹ ባሪክ ጎልድ እና ቢ 2 ጎልድ፣ የአውስትራሊያው ሬሶሉት ማይኒንግ እና የብሪታኒያው ሃሚንግበርድ ሪሶርስ፣ አሁንም የማዕድን ማውጣት ሥራቸው ሳይስተጓጎል ቀጥለዋል።

የወርቅ ማዕድን ማውጫ ሥፍራዎች በአፍሪቃ በየጊዜው የሞት አደጋ የሚያስከትል የመሬት መንሸራተት በተደጋጋሚ የሚደርስባቸው መሆናቸው፤ ባለሥልጣናቱ የከበሩ ማዕድናት ቁፋሮ ሥራዎችን ለመቆጣጠር የሚያደርጉትን ጥረት ፈታኝ አድርጎታል።

ከዓለም ድሃ አገሮች ተርታ የምትመደበው ማሊ፣ በወርቅ ምርቷ ከአፍሪካ በቀደሚ ደረጃ ካሉት አገራት አንዷ ነች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG