በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የማሊ መሪዎች የመንግሥታቱ ድርጅት ቃል አቀባይ እንዲወጡ አዘዙ


ፎቶ ፋይል፦ በባማኮ፣ ማሊ
ፎቶ ፋይል፦ በባማኮ፣ ማሊ

በማሊ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ልዑክ ቃል አቀባይ ኦሊቨር ሳልጌዶ በ72 ሰዓት ውስጥ አገሪቱን ለቅቀው እንዲወጡ ወታደራዊው መንግሥት አዘዘ።

ትዕዛዙ የተሰጠው ቃል አቀባዩ “የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተጠባባቂ ጦርን ለመርዳት 49 የአይቮሪ ኮስት ወታደሮች ማሊ መግባታቸውን በሚመለከት የማሊ መንግሥት ቀደም ብሎ መረጃ ደርሶታል” ሲሉ የትዊት በማድረጋቸው እንደሆነ ተገልጿል።

ወታደሮቹ የተያዙት ባለፈው ሐምሌ 3 ባማኮ አይሮፕላን ማረፊያ እንደደረሱ መሆኑ ተመልክቷል። ሳልጌዶ የተባበረሩት “አግባብ ያልሆነ መልዕክት በማስፈራቸው ነው” ሲል የማሊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በማኅበራዊ ገፁ ላይ ፅፏል።

የማሊ መንግሥት የወታደሮቹን መግባት አስቀድሞ እንደማያውቅ አመልክቷል።

ይሁን እንጂ መንግሥት ወታደሮቹ በተያዙበት ማግስት ሐምሌ 4 ባወጣው መግለጫ “ቅጥረኛ ተዋጊዎች” ሲል የጠራቸው ወታደሮች ወደ ማሊ የተላኩት “የማሊ ደኅንነት እንደገና የተዋቀረበትን መሠረትና ፀጥታ ለማናጋት ነው” ብሏል።

ሳልጌዶ ባሰፈሩት ትዊት ወታደሮቹ “ለአንደኛው የመንግሥታቱ ተጠባባቂ ጦር ክፍል የሎጂስቲክስ ድጋፍ ለመስጠት የመጡ እንጂ በማሊ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተጠባባቂ ኃይል (ሚኑስማ) አካልነታቸው አልነበረም” ብለዋል።

XS
SM
MD
LG