በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩክሬን ላይ ተመትቶ የወደቀውን የማሌዥያ አየር መንገድ ጄት ምርመራ ውጤት ይፋ ሆነ


እኤአ በ2014 ዩክሬን ላይ ተመትቶ የወደቀውን የማሌዥያ አየር መንገድ ጄት ጉዳይ እየመረመረ ያለው በኔዘርላንድስ የሚመራ መርማሪ ቡድን ሦስት ሩስያውያንና አንድ ዩክሬይናዊ በነፍስ መግደል ተጠርጣሪነት ይፋ አደረገ።

የኔዘርላንድስ ዋና ዐቃቤ ህግ ዛሬ ዘሄግ ላይ ባደረጉት ጋዜጣዊ ጉባዔ የበረራ ቁጥር ኤም ኤች 17 የመንገደኞች አውሮፕላን የተመታው በነዚህ ተጠርጣሪዎች አድራጎት ነው ብለዋል። አያይዘውም ድርጊቱን እነሱ ባይስቡትም፣ አውሮፕላኑ የተመታበትን ሚሳይል ላውንቸር አፈላልጎ በማግኘት በቅርበት ተባብረዋል ብለዋል።

ተጠርጣሪዎቹ ሩስያውያኑ ኢጎር ጊርኪን ሰርጌይ ዱቢኒስኪ እና ኦሌግ ፑላቶቭ ዩክሬይናዊው ደግሞ ሊዮኒድ ካርቼንኮ የሚባል መሆኑን ነው ዐቃቤ ህጉ የገለፁት።

ከአምስተርዳም ተነስቶ ወደማሌዥያ ኩዋላላምፑር ሲበር በሚሳይል በተመታው አውሮፕላን ውስጥ የነበሩት፣ 298ቱም ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG