በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማሌዢያ ላለፉት አስር አመታት የተሰወረውን አውሮፕላን ፍለጋ ልትጀምር ትችላለች


ማሌዢያ ላለፉት አስር አመታት የተሰወረውን አውሮፕላን መታሰቢያ በተዘጋጀው ሰሌዳ ላይ መልእክቱን እያሰፈረ ኩዋላ ላምፑር፣ ማሌዥያ እ አአአ እሑድ መጋቢት 3/2019
ማሌዢያ ላለፉት አስር አመታት የተሰወረውን አውሮፕላን መታሰቢያ በተዘጋጀው ሰሌዳ ላይ መልእክቱን እያሰፈረ ኩዋላ ላምፑር፣ ማሌዥያ እ አአአ እሑድ መጋቢት 3/2019

የዩናይትድ ስቴትስ የቴክኖሎጂ ኩባንያ፣ የማሌዢያ አየር መንገድ አውሮፕላን ከአሥር ዓመት በፊት ተከስክሶበታል ተብሎ በሚታመንበት ደቡባዊ ህንድ ውቅያኖስ ላይ አዲስ ፍለጋ እንዲካሄድ ሐሳብ ማቅረቡን ተከትሎ፣ የማሌዢያ መንግሥት የኤም ኤች 370 አውሮፕላን ፍለጋውን እንደአዲስ ሊጀምር እንደሚችል አስታውቋል።

መቀመጫውን በቴክሳስ ያደረገው 'ኦሽን ኢንፊኒቲ' የተሰኘ ተቋም "ካልተገኘ አይከፈልም" በሚል ስምምነት እንደአዲስ ባህሩን ለመፈተሽ ሀሳብ ማቅረቡን የትራንስፖርት ሚኒስትሩ አንተኒ ሎክ ተናግረዋል። ሚኒስትሩ አክለው ከድርጅቱ ጋር ለመገናኘት እና የአውሮፕላኑን የመጨረሻ ማረፊያ ስፍራ ለማግኘት የሚረዱትን አዳዲስ ሳይንሳዊ መረጃዎች ለመገምገም ግብዣ ማቅረባቸውን ገልጸዋል።

ማስረጃው ተዓማኒነት ያለው ሆኖ ከተገኘ፣ ከኦሽን ኢንፊኒቲ ጋር አዲስ ውል መፈራረም እና ፍለጋውን መቀጠል የሚያስችል ፍቃድ ከካቢኔያቸው እንደሚጠይቁም ሚኒስትሩ አመልክተዋል።

አውሮፕላኑ የተሰወረበትን አስረኛ ዓመት ለማክበር በተዘጋጀ መታሰቢያ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ሎክ "መንግስት ኤም ኤች 370ን ለማግኘት ፅኑ አቋም አለው" ያሉ ሲሆን "ፍለጋው አውሮፕላኑ ያለበትን አግኝቶ የሚወዷቸውን ላጡ ዘመድ አዝማዶች እውነቱን ያቀርባል የሚል ተስፋ አለን" ብለዋል።

እ.አ.አ መጋቢት 8፣ 2014 ዓ.ም በአብዛኛው የቻይና ዜግነት ያላቸው 239 ስዎች አሳፍሮ ከማሌዢያ ዋና ከተማ ኩላ ላምፑር የተነሳው እና ወደ ቤይጂንግ ይጓዝ የነበረው ቦይንግ 777፣ ከራዳር እይታ ውጪ የሆነው በረራ በጀመረ በደቂቃዎች ውስጥ ነበር። የሳተላይት መረጃ አውሮፕላኑ ከበረራ መስመሩ መውጣቱን ያመለከተ ሲሆን፣ ማናልባትም በደቡባዊ ህንድ ውቂያኖስ ላይ ተከስክሶ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለ።

ኦሽን ኢንፊኒቲ እ.አ.አ በ2018 ያካሄደው ፍለጋ አውሮፕላኑ የት እንደደረሰ የሚይሳይ ምንም ፍንጭ ሳያገኝ ቀርቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG