ዋሺንግተን ዲሲ —
ናጂብ ዛሬ በሀገሪቱ ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኃይሎች አቤታቸው እንዳሉ መያዛቸው ታውቋል። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር የተያዙት ሲአርሲ ኢንተርናሽናልና /IMDB/ በተባሉት ተቋማት ላይ ከሚደረገው ምርመራ ጋር በተያይዘ ነው ተብሏል።
ናጂብ ራዛክ ነገ በኦፊሴል ክስ ይቀርብባቸዋል። /IMDB/ ሥልጣን ላይ እንዳሉ የከፈቱት ሲሆን $4.5 ቢልዮን ዶላር ከተቋሙ ተዘርፏል ይላል የዩናይትድ ስቴትስ የፍርድ ሚኒስቴር። ከተዘረፈው ገንዘብ የተወሰነው በናጂብ የግል ባንክ ሂሳብ ገብቷል የሚል ነው ክሱ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ