በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የማላዊ ምርጫ


የማላዊ ህዝብ ዛሬ ፕሬዚዳንቱንና የፓርላማ ተወካዮቹን ምርጫ ሲያካሂድ ውሉዋል። ፕሬዚዳንቱ ፒተር ሙታሪካ ለሁለተኛ የሥልጣን ዘመን በዕጩነት ቀርበዋል።

ስድስት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን የሚሆነው የማላዊ መራጭ ከሰባ ስምንት ዓመቱ ሙታሪካ ከምክትል ፕሬዚዳንታቸው ሳኡሎስ ቺሊማ ወይም ከቀድሞው ሰባኪ ከላዛሩስ ቻክዌራ መሃል አንዱን ይመርጣሉ። ሃገሪቱን የወረሳትን ሙስና እንጠፋለን ብለው ቃል ገብተዋል።

ፕሬዚዳንት ሙታሪካ ደግሞ በምርጫ ዘመቻቸው የኢኮኖሚ እና የመሰረተ ልማት ማሻሻያ መርኃ ግብሮች አካሂዳለሁ ብለዋል።

ምክትል ፕሬዚዳንት ቺሊማ ከገዢው ዲሞክራሲያዊ ተራማጅ ፓርቲ ባለፈው ዓመት ወጥተው ከግማሽ ቢሊዩን የድምፅ ሰጪ ቁጥር የሚይዘው ወጣቱ ላይ ያተኮረ ፓርቲ አቋቁመዋል።

ከሙታሪካ በፊት የነበሩት ፕሬዚደንት ጆይስ ባንዳ ድጋፋቸውን ሰጥተዋቸው እንደነበርም ይታወሳል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG